ሩት 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፥ ዘወርም አለ፣ እነሆም፥ አንዲት ሴት በእግርጌው ተኝታ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኩለ ሌሊት ላይ ሰውየውን አንዳች ነገር አስደነገጠው፤ ገልበጥ ሲልም አንዲት ሴት እግርጌው ተኝታ አገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፥ ዘወርም አለ፥ እነሆም፥ አንዲት ሴት በግርጌው ተኝታ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እኩለ ሌሊት ገደማም ቦዔዝ ድንገት ነቅቶ ሲገላበጥ አንዲት ሴት በግርጌ ተኝታ በማግኘቱ ተደነቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፤ ዘወርም አለ፤ እነሆም፥ አንዲት ሴት በእግርጌው ተኝታ ነበረች። |