ሩት 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተኛም ጊዜ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም እግሩን ግለጪ፥ ተጋደሚም፣ የምታደርጊውንም እርሱ ይነግርሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተኛም ጊዜ፣ የሚተኛበትን ቦታ ልብ ብለሽ እዪና ሄደሽ እግሩን ገልጠሽ ተኚ፤ ከዚያም የምታደርጊውን ራሱ ይነግርሻል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚተኛም ጊዜ፥ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም ከግርጌው በኩል ልብሱን ገልጠሽ በእግሩ አጠገብ ተኚ፤ ምን ማድረግ እንደሚገባሽ እርሱ ራሱ ይነግርሻል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የት እንደሚተኛ ካረጋገጥሽ በኋላ፥ እንቅልፍ ሲወስደው ወደ እርሱ ቀረብ በዪና ከግርጌው በኩል ልብሱን ገልጠሽ በእግሩ አጠገብ ተኚ፤ ምን ማድረግ እንደሚገባሽ እርሱ ራሱ ይነግርሻል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትኛም ጊዜ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፤ ገብተሽም እግሩን ግለጪ፤ ተጋደሚም፤ የምታደርጊውንም እርሱ ይነግርሻል።” |