ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆነውን፥ የተመረጠውን፥ የከበረውንና መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
ሩት 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሰውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና ፍጻሜው እስኪታወቅ ድረስ ዝም በዪ አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑኃሚንም፣ “ልጄ ሆይ፤ የሚሆነውን ነገር እስክታውቂ ድረስ ታገሺ፤ ጕዳዩ ዛሬውኑ እልባት ካላገኘ ሰውየው አያርፍም” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም፦ “ልጄ ሆይ! ሰውዬው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና፥ ፍጻሜው እስኪታወቅ ድረስ ጠብቂ” አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚም “ልጄ ሆይ! ሰውዬው ይህን ነገር ዛሬ እስኪፈጽም ድረስ አያርፍምና፥ ፍጻሜው እስኪታወቅ ድረስ ጠብቂ” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም “ልጄ ሆይ! ስውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና ፍጻሜው እስኪታወቅ ድረስ ዝም በዪ፤” አለች። |
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆነውን፥ የተመረጠውን፥ የከበረውንና መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።