ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።
ሩት 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፥ አማትዋም የቃረመችውን አየች፣ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያንም ይዛ ወደ ከተማ ሄደች፤ ዐማቷም የሰበሰበችው ምን ያህል እንደ ሆነም አየች፤ እንዲሁም ሩት የሚበቃትን ያህል ከበላች በኋላ አስተርፋ የነበረውን አውጥታ ለርሷ ሰጠቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፥ አማትዋም የቃረመችውን አየች፥ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እህሉንም ተሸክማ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ምን ያኽል እንደ ሰበሰበችም ለዐማትዋ አሳየቻት፤ ከምሳዋ ተርፎአት የነበረውንም ምግብ ሰጠቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፤ አማትዋም የቃረመችውን አየች፤ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። |
ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።
በምሳም ጊዜ ቦዔዝ፦ ወደዚህ ቅረቢ፣ ምሳ ብዪ፥ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሽ አላት። በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች የተጠበሰም እሸት ሰጣት፥ በልታም ጠገበች፥ አተረፈችም።