ሩት 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፣ የቃረመችውንም ወቃችው፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሩት እስኪመሽ ድረስ ከአዝመራው ላይ ቃረመች፤ ከዚያም የሰበሰበችውን ገብስ ወቃች፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያም ያህል ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፥ የቃረመችውንም ወቃችው፥ ዐሥር ኪሎ ያህልም ገብስ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሩትም እስከ ምሽት ድረስ ከእርሻው እህል ስትቃርም ዋለች፤ ባሸችውም ጊዜ ዐሥር ኪሎ ያኽል ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፤ የቃረመችውንም ወቃችው፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ። |