አሁንም እግዚአብሔር ምሕረትንና ጽድቅን ያድርግላችሁ፤ ይህንም ነገር አድርጋችኋልና እኔ ደግሞ ይህን በጎነት እመልስላችኋለሁ።
ሩት 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑኃሚንም ምራቶችዋን፦ ሂዱ፥ ወደ እናቶቻችሁም ቤት ተመለሱ፣ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችሁ፥ እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኑኃሚን ሁለቱን ምራቶቿን እንዲህ አለቻቸው፤ “እያንዳንዳችሁ ወደ እናቶቻችሁ ቤት ተመለሱ፤ ለሞቱ ባሎቻችሁና ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረጋችሁ፣ ለእናንተም እግዚአብሔር እንደዚሁ ያድርግላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዖሚም ምራቶችዋን፦ “ሂዱ፥ ወደ እናቶቻችሁም ቤት ተመለሱ፥ ለእኔና ለሞቱት እንዳደረጋችሁት፥ ጌታም ቸርነት ያድርግላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚ ምራቶችዋን እንዲህ አለቻቸው፤ “እንግዲህ ወደየቤታችሁ ተመለሱና ከእናቶቻችሁ ጋር ኑሩ፤ ለእኔና ለሟቾቹ ባሎቻችሁ መልካም ነገር እንዳደረጋችሁ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም ነገር ያድርግላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑኃሚንም ምራቶችዋን “ሂዱ፤ ወደ እናቶቻችሁም ቤት ተመለሱ፤ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችሁ፥ እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችሁ። |
አሁንም እግዚአብሔር ምሕረትንና ጽድቅን ያድርግላችሁ፤ ይህንም ነገር አድርጋችኋልና እኔ ደግሞ ይህን በጎነት እመልስላችኋለሁ።
ኑኃሚንም ምራትዋን፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ፦ ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት።
ቦዔዝም አላት፦ ልጄ ሆይ፥ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፣ ባለጠጋም ድሀም ብለሽ ጐበዛዝትን አልተከተልሽምና ከፊተኛው ይልቅ በመጨረሻው ጊዜ ቸርነት አድርገሻል።