ሩት 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፦ ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን አሉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥለውም፣ “አይሆንም! ከአንቺ ጋራ ተመልሰን ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን” አሏት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን” አሉአት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አይሆንም! እኛ ከአንቺ ጋር ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን” አሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም “ከእንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን፤” አሉአት። |
የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።