ሮሜ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከርሞ እንደ ዛሬ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ታገናለች፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” ተብሎ ተስፋው ተሰጥቷልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የተስፋው ቃል “በዚህ ጊዜ እመጣለሁ ሳራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤” የሚል ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም እግዚአብሔር የሰጠው የተስፋ ቃል “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ እመጣለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” የሚል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ፦ በዚህ ጊዜ እመጣለሁ ለሳራም ልጅ ይሆንላታል የሚል የተስፋ ቃል ነውና። |
በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”
አሁንም እላችኋለሁ፥ ከእነዚህ ሰዎች ራቁ፤ ተዉአቸውም፤ ይህ ምክራቸው፥ ይህም ሥራቸው ከሰው የተገኘ ከሆነ ያልፋል ይጠፋልም።