ትዕግሥትም መከራ ነው፤ በመከራም ተስፋ ይገናል።
ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤
ጽናትም የተፈተነ ባሕርይን ያስገኝልናል፥ የተፈተነ ባሕርይም ተስፋን፤
ከትዕግሥትም በፈተና መጽናት፥ ከመጽናትም ተስፋ ይገኛል።
ከአራጣና ከቅሚያ ነፍሳቸውን ያድናታል፤ ስሙም በፊታቸው ክቡር ነው።
በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ገንዘብ ታደርጓታላችሁ።
የተጻፈው ሁሉ በመታገሣችንና መጻሕፍትን በመታመናችን ተስፋችንን እናገኝ ዘንድ እና ልንማርበት ተጻፈ።
ልጅ አባቱን እንደሚያገለግል፥ በወንጌል ትምህርት እንደ አገለገለኝ፥ የዚህን ሰው ጠባዩን ታውቃላችሁ።
ይህችም ተስፋ ነፍሳችን እንዳትነዋወጥ እንደ መልሕቅ የምታጸና ናት፤
በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችሁማል፤ ያበረታችሁማል።