ሮሜ 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንድ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁም በክርስቶስ መታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ይጸድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። |
ስለዚህም በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ፤ እንደዚሁም ሁሉ ኀጢአትን ስለ አደረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋው በበደላችን መጠን የሆነብን አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ከሞቱ፥ እንግዲህ በእግዚአብሔር ጸጋ፥ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በሰጠን ሀብቱ ሕይወት በብዙዎች ላይ እንዴት እጅግ ይበዛ ይሆን?