ሮሜ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚሠራ ዋጋው እንደሚገባው እንጂ በለጋስነት እንደ ሰጡት ሆኖ አይቈጠርበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ሥራ ከሠራ ደመወዙ እንደ ስጦታ ሳይሆን እንደ ተገቢ ዋጋው ይቈጠርለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ለሚሠራ ሰው፥ ደመወዝ እንደ ክፍያ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቆጠርለትም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሠራ ሰው የሚያገኘው ደመወዝ ተገቢ የጒልበቱን ዋጋ ነው እንጂ ስጦታ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቍኦጠርለትም፤ |
ይህስ ስለምን ነው? ጽድቃቸው የኦሪትን ሥራ በመሥራት እንጂ በእምነት ስለ አልሆነ ነው፤ የእንቅፋት ድንጋይ አሰነካከላቸው።