ሮሜ 4:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ኀጢአታችን የተሰቀለውን፥ ሊያስነሣንና ሊያጸድቀን የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ በአስነሣው ስለምናምን ስለ እናም ነው እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ ለሚቈጥርልን፣ ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በርሱ ለምናምን ለእኛም ጭምር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእኛም ጭምር ነው፤ ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛም እንዲቆጠርልን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኛም ጭምር ነው፤ ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ባስነሣው አምላክ ለምናምን ለእኛም እምነታችን ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርልናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቍኦጠርልን ዘንድ አለው። |