ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች መነሣሣት ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል” አለው።
ሮሜ 2:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተጻፈም “እነሆ፥ በእናንተ ምክንያት አሕዛብ የእግዚአብሔርን ስም ይሰድባሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ዘንድ ይሰደባል” ተብሎ እንደ ተጻፈው መሆኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በሕዝቦች መካከል ይሰደባልና” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም፥ “በእናንተ በአይሁድ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ዘንድ ይሰደባል” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ። |
ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች መነሣሣት ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል” አለው።
ሕዝቤ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አቆማችሁ?” ይላል እግዚአብሔር፤ “ታደንቃላችሁ፤ ትጮሃላችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ስሜም በእናንተ ምክንያት በአሕዛብ ዘንድ ሁልጊዜ ይሰደባል።
“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ቤት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህም ደግሞ አባቶቻችሁ በአደረጉት ዐመፅ አስቈጡኝ።
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤
የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።