Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኦሪ​ት​ንም ብት​ፈ​ጽም ግዝ​ረት ትጠ​ቅ​ም​ሃ​ለች፤ ኦሪ​ትን ባት​ፈ​ጽም ግን ግዝ​ረ​ትህ አለ​መ​ገ​ዘር ትሆ​ን​ብ​ሃ​ለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሕግን የምትፈጽም ከሆነ ግዝረት ዋጋ አለው፤ ሕግን የምትተላለፍ ከሆነ ግን እንዳልተገረዝህ ሆነሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሕግን የምትፈጽም ከሆነ መገረዝ ይጠቅማል፤ ሕግን የምትተላለፍ ከሆነ ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ሆኖአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 መገረዝ በእርግጥ የሚጠቅምህ ሕግን ብትፈጽም ነው፤ ሕግን የምታፈርስ ከሆነ ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይቈጠራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሕግን ብታደርግ መገረዝስ ይጠቅማል፤ ሕግን ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ አለ መገረዝ ሆኖአል።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 2:25
16 Referencias Cruzadas  

እና​ን​ተም የይ​ሁዳ ሰዎች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ወጣ የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ውም ሳይ​ኖር እን​ዳ​ይ​ነድ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ተገ​ረዙ፤ የል​ባ​ች​ሁ​ንም ሸለ​ፈት አስ​ወ​ግዱ።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም።


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል።


በውኑ ለሰው ይም​ሰል አይ​ሁ​ዳዊ መሆን ይገ​ባ​ልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገ​ዘ​ሩ​አ​ልን?


በኦ​ሪት ትመ​ካ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ኦሪ​ትን በመ​ሻር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቃ​ል​ለ​ዋ​ለህ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሕግን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ይጸ​ድ​ቃሉ እንጂ ሕግን የሚ​ሰሙ አይ​ጸ​ድ​ቁ​ምና።


አንተ ሳት​ገ​ዘር ብት​ኖር፥ ኦሪ​ት​ንም ብት​ጠ​ብቅ አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ መገ​ዘር ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።


ተገ​ዝ​ረህ ኦሪ​ትን ከም​ታ​ፈ​ርስ በተ​ፈ​ጥሮ ያገ​ኘ​ሃት አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ አብ​ራህ ብት​ኖር ይሻ​ል​ሃል፤ ኦሪ​ትን ከም​ታ​ፈ​ርስ ከአ​ንተ ከተ​ገ​ዘ​ር​ኸው ያ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረው፥ ኦሪ​ትን የሚ​ፈ​ጽ​መው ይሻ​ላል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ መጠ​በቅ ነው እንጂ መገ​ዘ​ርም አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም አይ​ጎ​ዳም።


የተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም ቢሆኑ በሰ​ው​ነ​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​መኩ ልት​ገ​ዘሩ ይወ​ዳሉ እንጂ ኦሪ​ትን አል​ጠ​በ​ቁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios