ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጕር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ወደ ቆዳው ባይጠልቅ፤ ይላጫል፤
ሮሜ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኦሪት ትመካለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ኦሪትን በመሻር እግዚአብሔርን ታቃልለዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ በሕግ የምትመካ፣ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታዋርዳለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታዋርዳለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በእግዚአብሔር ሕግ ትመካለህ፤ ነገር ግን ሕጉን በማፍረስ እግዚአብሔርን ትንቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን? |
ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጕር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ወደ ቆዳው ባይጠልቅ፤ ይላጫል፤
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
ፈሪሳዊውም ቆመና እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማኞችና እንደ ዐመፀኞች፥ እንደ አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ያላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ።
እኔ በአብ ዘንድ የምከስሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከስሳችሁስ አለ፤ እርሱም እናንተ ተስፋ የምታደርጉት ሙሴ ነው።