ሮሜ 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስቀሪጦስን፥ አልሶንጳን፥ ሄርሜስን፥ ጳጥሮባስን፥ ሄርማስን፥ ከእነርሱ ጋር ያሉ ወንድሞቻችንንም ሰላም በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ፣ ለሄሮሜን፣ ለጳጥሮባን፣ ለሄርማን፣ ከእነርሱም ጋራ ላሉት ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ ለሄሮሜንም ለጳጥሮባም ለሄርማንም ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአስንክሪቶስና ለፍሌጎን፥ ለሄርሜስም፥ ለፓትሮባስም፥ ለሄርማስም፥ ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ ለሄሮሜንም ለጳጥሮባም ለሄርማንም ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
ልጁ በብዙዎች ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውንና የመረጣቸውን እነርሱን ልጁን ይመስሉ ዘንድ አዘጋጅቶአቸዋል።
በቈላስይስ ላሉ ቅዱሳንና በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ወንድሞቻችን፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
አሁንም ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞቻችን ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ።