ሮሜ 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መልካም ለሚሠራ የሚአስፈሩ አይደሉም፤ ሹሞችን እንዳትፈራ ብትፈልግ መልካም አድርግ፤ እነርሱ ደግሞ ያመሰግኑሃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዦች ክፉ ለሚሠሩ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያስ መልካሙን አድርግ፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ አድራጊዎችን እንጂ መልካም አድራጊዎችን አይደለም፤ ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ መልካሙን ነገር አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤ |
ለባለሥልጣን አልገዛም ያለ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንቢ ማለቱ ነው፤ መገዛትን እንቢ የሚሉም በራሳቸው ላይ ቅጣትን ያመጣሉ።
አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።