ሮሜ 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጸጋ ከጸደቁ ግን በሥራቸው አይደለማ፤ በሥራም የሚጸድቁ ከሆነ ጸጋ ጸጋ አይባልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ በጸጋ ከሆነ በሥራ አይደለም፤ በሥራ ቢሆንማ ኖሮ ጸጋ፣ ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጸጋ ከሆነ ግን በሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ያለዚያ ጸጋ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምርጫው በጸጋ ከሆነ በሥራ አይደለም ማለት ነው፤ በሥራ ከሆነማ፥ ጸጋ ዋጋቢስ በሆነ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል። |
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለሁበት አለሁ፤ ለእኔም የሰጠኝ ጸጋው ለከንቱ የሆነብኝ አይደለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደረው የእግዚአብሔር ጸጋ አጸናኝ እንጂ እኔ አይደለሁም።
ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ፥ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤