ሮሜ 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀድሞ እናንተ እግዚአብሔርን እንደ አልታዘዛችሁት፥ ዛሬ ግን በእነርሱ አለመታዘዝ ይቅር እንዳላችሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ እንደ ነበራችሁ፣ ከእነርሱ አለመታዘዝ የተነሣ አሁን ምሕረት እንዳገኛችሁ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን በማይታዘዙት ምክንያት ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ አሕዛብ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ ነበራችሁ፤ አሁን ግን አይሁድ ባለመታዘዛቸው ምክንያት እናንተ የእግዚአብሔርን ምሕረት አገኛችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን ከአለመታዘዛቸው የተነሣ ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ |
አሕዛብም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ይቅር ብሎአቸዋልና፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል እገዛልሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።”
ስለ ደናግልም የምነግራችሁ የእግዚአብሔር ትእዛዝ አይደለም፤ ታማኝ እንድሆን እግዚአብሔር ይቅር ያለኝ እንደ መሆኔ ምክሬን እነግራችኋለሁ እንጂ።
እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።