ሮሜ 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወደ ጥልቁም ማን ይወርዳል?” አትበል፤ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወይም ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል”፤ ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም “በልብህ ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል፤” ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማስነሣት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም በልብህ “ወደ ሲኦል ማን ይወርዳል?” አትበል፤ ይህም ክርስቶስን ከሞት ለማስነሣት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። |
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤