ራእይ 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈረሰኛው ሰራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር፤ ቍጥራቸውንም ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈረሰኞችም ጭፍራ ቍጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፈረሰኞቹ ሠራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን መሆኑን ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር እልፍ ጊዜ እልፍ፥ እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ። |
እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ መሳፍንትና መኳንንት፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ የተመረጡ ፈረሰኞች ነበሩ።
እመልስህማለሁ፤ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፤ አንተንና ሠራዊትህን ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን፥ የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን፥ ሰይፍንም የያዙትን ሁሉ አወጣለሁ።
አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤