ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፤ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፤
ራእይ 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ወደዚህ ና፤ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ፤” ብሎ ተናገረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባቱ የመጨረሻ መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፣ “ና፤ የበጉ ሚስት የሆነችውን ሙሽራ አሳይሃለሁ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባቱ የመጨረሻዎቹ መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ወደዚህ ና፤ የበጉን ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ፤” ብሎ ተናገረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና! የበጉ ሚስት የሆነችውን ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ ወደዚህ ና፥ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ ብሎ ተናገረኝ። |
ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፤ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፤
እርሱም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”