በሰው ደም የሚገባ ዐመፀኛ ሰው ወደ ጕድጓድ በሚገባበት ጊዜ የሚይዘው የለም፥ ለነፍሰ ገዳይም ዋስ የሚሆን ሰው ይሰደዳል፥ በደኅናም አይኖርም። ልጅህን አስተምረው ይወድድሃልም፥ ለነፍስህም ክብርን ይሰጣል። ዐመፀኛ ሕዝብ ሕግን አይሰማም።