የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
የአገልጋይህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
አምላክ ሆይ! ጸሎቴን ወደ ላይ ወደ አንተ ስለማሰማ እኔን አገልጋይህን ደስ አሰኘኝ።
አፋቸው ከንቱ ነገርን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የዐመፃ ቀኝ ከሆነ አስጥለኝ።
አቤቱ፥ እኔ በየዋህነቴ እኖራለሁና ፍረድልኝ፤ እንዳልደክም በእግዚአብሔር አመንሁ።
ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
ነገር ግን በውስጥዋ ደስታንና ሐሤትን ያገኛሉ፤ እኔም ለኢየሩሳሌም ደስታን ለሕዝቤም ሐሤትን አደርጋለሁ።