የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆናልና ማንም፦ ይህች ኤልዛቤል ናት ይል ዘንድ አይችልም ብሎ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው” አለ።
መዝሙር 83:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክ ምጽዋትንና እውነትን ይወድዳልና፥ እግዚአብሔር ክብርና ሞገስን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከበረከቱ አያሳጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣ መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጉድፍ ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዖሬብና በዜብ ላይ ያደረግኸውን በእነርሱም መሪዎች ላይ አድርግ፤ በዜባሕና በጻልሙናዕ ያደረግኸውን በእነርሱም ገዢዎች ላይ አድርግ። |
የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆናልና ማንም፦ ይህች ኤልዛቤል ናት ይል ዘንድ አይችልም ብሎ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው” አለ።
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
የምድያምን ሁለቱን አለቆች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬብንም በሱርኤራብ ገደሉት፥ ዜብንም በኢያፌቅ ገደሉት፤ የምድያምንም ሰዎች አሳደዱ፤ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ጌዴዎን አመጡ።