ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
የእስረኞች ሰቈቃ በፊትህ ይድረስ፤ በክንድህም ብርታት፣ ሞት የተፈረደባቸውን አድን።
የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፥ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።
የእስረኞች መቃተት ወደ አንተ እንዲደርስ አድርግ፤ ሞት የተፈረደባቸውንም በታላቁ ኀይልህ አድናቸው።
ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኀያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
አቤቱ፥ ማረን፤ አንተን ተማምነናልና፤ የዐላውያን ዘራቸው ለጥፋት ነው፤ በመከራም ጊዜ መድኀኒታችን አንተ ነህ።
የዕውራንንም ዐይን ትከፍት ዘንድ፥ የተጋዙትንም ከግዞት ቤት፥ በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።
ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’
በከሃሊነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የምናስበውንና የምንለምነውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበዙም ዘንድ ሊያጸናችሁ ለሚችል፥