መዝሙር 76:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፥ ምድር ፈራች ዝምም አለች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በምድር የተጨቈኑትን ሁሉ ለመቤዠት፥ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ዓለም ጸጥ አለ። |
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፣ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።
እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም፥ “ሦስታችሁ ወደ ምስክሩ ድንኳን ኑ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወደ ምስክሩ ድንኳን ወጡ።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።