እንደ ላይኛው መንገድ፥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በገጀሞ በሮችዋን ሰበሩ።
በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤ እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።
እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም፤ በሌሎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ በእነርሱ ላይ አይደርስም።
ኀጢአተኛውን ክፉ ቀን ትጠብቀዋለች፤ በቍጣ ቀንም ይወስዱታል።
እኔ ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፤ ጻዕርም ሥጋዬን ይይዛል።
ቤታቸው በብልፅግና የተሞላ ነው፤ የሚያስፈራቸውም የለም። ከእግዚአብሔርም ዘንድ መቅሠፍት አይመጣባቸውም።
እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ።
ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን በጌታ እንገሠጻለን።
ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና፥ ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።