“ነፍሴን የምትነዘንዙአት፥ በቃላችሁስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገብኝ ዕወቁ፤
መዝሙር 72:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሞታቸው እረፍት የለውምና፤ ለመቅሠፍታቸውም ኀይል የለውምና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤ የድኾችን ልጆች ያድናል፤ ጨቋኙንም ያደቅቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ይፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች ያድን፥ ጨቋኙንም ይጨፍልቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቡ መካከል ለተጨቈኑት ፍርድን ይስጥ፤ ችግረኞችንም ይርዳ፤ ጨቋኝንም ይደምስስ |
“ነፍሴን የምትነዘንዙአት፥ በቃላችሁስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገብኝ ዕወቁ፤
እግዚአብሔር ወደ ታች ወደ ሰዎች ይመለከታል፥ ሊመረመሩ የማይችሉ ነገሮችን ሁሉ፥ ቍጥር የሌላቸውን የተከበሩትንና ድንቆችንም ያስተውላል።
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።
እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፣ የአንዲቱን ስም ውበት የሁለተኛይቱንም ስም ማሰሪያ ብዬ ጠራሁ፣ መንጋውንም ጠበቅሁ።