እንዲህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁአትን?” እጆቼንም በንጽሕና አጠብሁ።
ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ድኾችንም ከሞት ያድናል።
ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።
ለድኾችና ለደካሞች ይራራል፤ በችግር ላይ ያሉትንም ሰዎች ከሞት ያድናል።
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”
“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።
“ንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።