መዝሙር 68:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥ እፍረትም ፊቴን ሸፍኖኛልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፣ በምድረ በዳም በተጓዝህ ጊዜ፣ ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፥ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፥ በበረሓም አብረሃቸው በተጓዝህ ጊዜ፥ |
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።
አምላካችን እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ማስፈራራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥
ዲቦራም ባርቅን፥ “እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ይሄዳል” አለችው። ባርቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።
አቤቱ! ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፤ ሰማያትም ጠልን አንጠባጠቡ፤ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠባጠቡ።