መዝሙር 41:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራዋለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤ እንዲህ እያሉም፣ የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን ለመጠየቅ የሚገባ ከንቱን ይናገራል፥ ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት፥ ወደ ውጭ ይወጣል ይናገራልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚጠሉኝ ሁሉ በእኔ ላይ በሹክሹክታ ይናገራሉ፤ ክፉ ነገር እንዲደርስብኝም ያቅዳሉ። |
እነርሱም ዐመፅን ሁሉ፥ ክፋትንም፥ ምኞትንም፥ ቅሚያንም፥ ቅናትንም የተመሉ ናቸው፤ ምቀኞች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ከዳተኞች፥ ተንኰለኞች፥ ኩሩዎች፥ ጠባያቸውንና ግብራቸውንም ያከፉ ናቸው።
ነገር ግን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ እንደምወደው ሆናችሁ ያላገኘኋችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እንደማትወዱት እሆንባችኋለሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ወይም እኮ በመካከላችሁ ክርክር፥ ኵራት፥ መቀናናት፥ መበሳጨት፥ መዘባበት፥ ወይም መተማማት፥ መታወክ፥ ወይም ልብን ማስታበይ ይኖር ይሆናል።