በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
መዝሙር 40:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቼም ሁሉ ይጠቃቀሱብኛል፥ በእኔ ላይም ክፋትን ይመክራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ መጥቻለሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ተጽፏል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሥዋዕትንና ቁርባንን አልወደድህም፥ የሚሰማ ጆሮ ሰጠኸኝ፥ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “ስለ እኔ በተጻፈው የሕግ መጽሐፍ መሠረት እነሆ እኔ መጥቻለሁ። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
እርሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ እንዳለው፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ የነገርኋችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላቸው።
መጻሕፍትን መርምሩ፤ በእነርሱ የዘለዓለም ሕይወትን የምታገኙ ይመስላችኋልና፤ እነርሱም የእኔ ምስክሮች ናቸው።
ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።