የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ይሁን፥ ይሁን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፥ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።
ድሃውን ከሚቀማው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።