መዝሙር 32:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈጠሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ ማስተዋል እንደሌላቸው፣ እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲገቱ ለማድረግ በልባብና በልጓም እንደሚመሩት እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ። እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም። |
“ኤፍሬም ሲጨነቅ መስማትን ሰማሁ፤ እንዲህም አለ፦ ቀጣኸኝ እኔም እንዳልቀና ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።
የሕዝቤ አለቆች አላወቁኝም፤ እነርሱ ሰነፎች ልጆች ናቸው፤ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፤ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።