እግዚአብሔርንም በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።
ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣ በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት፤
ጌታ በደልን የማይቈጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው።
እግዚአብሔር ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ከሽንገላም የራቀ ሰው የተባረከ ነው።
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የተመረጠ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ወይም የድኅነት መሥዋዕት ያደርገው ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ በሌላም ቦታ ቢያርደው፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአልና፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
ናትናኤልም፥ “በውኑ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻላልን?” አለው፤ ፊልጶስም፥ “መጥተህ እይ” አለው።
ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢአት ምን እንደ ሆነች ሳትታወቅ በዓለም ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን የኦሪት ሕግ ገና ስላልመጣ ኀጢአት ተብላ አትቈጠርም ነበር።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
በአፋቸውም ውሸት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውም።