መዝሙር 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋራ፣ ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋራ አታስወግዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤ ሕይወቴንም አታጥፋ። |
በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተከታታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ። እግዚአብሔርም አለ፥ “የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት፥”
እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?’ ይሉታል።
የሚያሳድድህና ነፍስህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌታዬ ነፍስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሕይወት ማሰሪያ የታሰረች ትሆናለች፤ የጠላቶችህ ነፍስ ግን በወንጭፍ እንደሚወነጨፍ ትሁን።