በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሸሽጎኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሰውሮኛልና፥ በዓለትም ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አልቀመጥም።
የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥ ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም።
የክፉ አድራጊዎችን ጉባኤ እጠላለሁ፤ ከክፉዎችም ጋር መቀመጥ አልፈቅድም።
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልያል፤ ነገር ግን ብዙ የጥፋት ውኃ ወደ አንተ አይቀርብም።