ለሚያስጨንቁኝ ፈቃድ አትስጠኝ፥ የዐመፅ ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፥ ሐሰትም የዐመፅ ራስ ነው።
እግሮቼ በደልዳላ ስፍራ ቆመዋል፤ በታላቅ ጉባኤ መካከልም እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ።
እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤ እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።
እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
የባለጠጎችን ስድብና የትዕቢተኞችን ውርደት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች።
አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝ፥ አድምጠኝም።
እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ አይሰጠውም።
በኀጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥ በጽድቅህም አይግቡ።
በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።
“ስምህን ለወንድሞች እነግራቸዋለሁ፤ በማኅበር መካከልም አመሰግንሃለሁ” አለ።
ለሚጸልይ ጸሎቱን ይሰጠዋል፤ የጻድቃንን ዘመን ይባርካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይደለምና።