በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።
የሞት ገመዶች ጠፍረው ያዙኝ፥ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፥
የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ።
አቤቱ፥ ለቸሮች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
እግዚአብሔር ግን የሞትን ማሰሪያ ፈቶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው፤ ሞት እርሱን ሊይዘው አይችልምና።