የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
እርሱ ብቻውን ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
እርሱ ብቻ ታላላቅ ተአምራትን ያደርጋል፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
እርሱ የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን የከበረና ድንቅ ነገር ያደርጋል።
ነገር ግን ስለ ሽንገላቸው አቈየሃቸው፥ በመነሣታቸውም ጣልኻቸው።
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።