የምስጋና መሥዋዕትም ይሠዉለት፥ በደስታም ሥራውን ይንገሩ።
እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ።
በዚያ ሳሉ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮችና፥ በቀይ ባሕርም ያደረገላቸውን አስገራሚ ነገሮች ዘነጉ።
እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ባጠፋቸው ነበር አለ።
ነፋስህን ላክህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በብዙ ውኆች ውስጥ እንደ አረር ሰጠሙ።