ሰውነታቸውም መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ።
በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባም ክፉዎችን አቃጠላቸው።
በተከታዮቻቸውም ላይ እሳት ወረደ፤ እነዚያንም ክፉ ሰዎች አቃጠለ።
ሙሴም አሮንን፥ “ጥናህን ውሰድ፤ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፤ ዕጣንም ጨምርበት፤ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው፤ አስተስርይላቸውም፤ ከእግዚአብሔር ፊት ቍጣ ወጥቶአልና፥ ሕዝቡንም ያጠፋቸው ዘንድ ጀምሮአል” አለው።
አምላካችን በእውነት የሚያቃጥል እሳት ነውና።