ከጠላቶቻቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላቶቻቸውም እጅ ተቤዣቸው።
ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ፣ ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጎ አጸናለት፤
ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን፥ ለእስራኤልም የዘለዓለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፥
ለያዕቆብ ሥርዓት፥ ለእስራኤልም ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አድርጎ አጸናው።
በውኑ ቤቴ በኀያሉ ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በዘመኑ ሁሉ የተዘጋጀና የተጠበቀ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፤ መድኀኒቴም ፈቃዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመፀኛም አይበቅልምና።
በዘለዓለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው፥