እግዝአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
ይብራ መሰልሁ፤ በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጕጕት ሆንሁ።
ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ።
ብቻውን በበረሓ እንደሚኖር እርኩምና በወና ቤት እንደሚኖር ጒጒት ሆኜአለሁ።
ቍርበቴ ከሥጋዬ ጋር ይበጣጠሳል። አጥንቶቼም ይፋጩብኛል።
እንደ ሸመላ እንዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤
ሰጎን በየወገኑ፤ ጠለቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፤
ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥
መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጥዋ ይመሰጋሉ፣ ይብራና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፣ ድምፃቸው በመስኮቶችዋ ይጮኻል፣ የዝግባም እንጨት ሥራ ይገለጣልና በመድረኮችዋ ላይ ጥፋት ይሆናል።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤