አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ ፊትህ ይድረስ።
ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ።
የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ እዘምራለሁ፤ አዜማለሁም።
ለተበደሉትም የሚፈርድላቸው፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታቸዋል፤
አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
አቤቱ፥ ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ።
ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ርኅራኄውንና ጭካኔውን አስተውል፤ የወደቁትን ቀጣቸው፤ አንተን ግን ይቅር እንዳለህ ብትኖር ማረህ፤ ያለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ።