ምሳሌ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ይበልጡን ጠቢብ ይሆናል፥ ጻድቅንም አስተምረው፥ ይበልጡን አዋቂ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቢብን አስተምረው፥ በይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ደግን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀትን ይጨምራል። |
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።