ጥበብን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸልም አትበሉት።
ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።
ትምህርቴን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ ቸል አትበሉትም።
የምትማሩትን አስተውሉ፤ ብልኆች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።
በግንብ ድምድማት ትሰብካለች፥ በኀያላን በሮች ታገለግላለች። በከተማ በሮች በድፍረት እንዲህ ትላለች፦
ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤
ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል። ተግሣጽን የሚወድድ ግን ራሱን ይወድዳል።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።
ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን ተመልከት፤ ጆሮህም ወደ ቃሌ ያድምጥ፥
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?