ምሳሌ 8:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓለምንም ፈጥሮ በፈጸመና ደስ ባለው ጊዜ፥ ደስታዬ በሰው ልጆች መካከል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርሱ በሆነው መላው ዓለም ሐሤት እያደረግሁ፣ በሰው ልጆች ደስ እሰኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስታዬም በምድሩ ተድላዬም በሰው ልጆች ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በፈጠረው ዓለም ደስ ይለኛል፤ በሰው ዘርም ሐሤት አደርጋለሁ። |
ከፋሲካ በዓል አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓለም ያሉትን የወደዳቸውን ወገኖቹን ፈጽሞ ወደዳቸው።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸርነቱን ታውቃላችሁ፤ በእርሱ ድህነት እናንተ ባለጸጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለጸጋ ሲሆን፥ ስለ እናንተ ራሱን ድሃ አደረገ።