እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
ምሳሌ 8:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርን ሳይፈጥር አስቀድሞ ከዓለም በፊት ሠራኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ፣ ከጥንት ከዘላለም ተሾምሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥንቱ ከዘለዓለም ጀምሮ ተሾምሁ ምድር ከመፈጠርዋ አስቀድሞ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓለም ከመፈጠርዋ አስቀድሞ፥ ከዘመናት በፊት ተሾምኩ። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
አባት ሆይ፥ የሰጠኸኝ እነዚህ እኔ ባለሁበት አብረውኝ ይኖሩ ዘንድና የሰጠኸኝን ክብሬን ያዩ ዘንድ እወድዳለሁ፤ ዓለም ሳይፈጠር ወድደኸኛልና።